“ካስፈለገ በድጋሚ ኢራንን እንመታለን” ኔታንያሁ

Date:

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እስራኤል ካስፈለገ በድጋሚ በኢራን ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር አስጠነቀቁ።

ኔታንያሁ ቴልአቪቭ በድጋሚ በኢራን ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር በመግለጽ፣ ቴህራን “የኒውክሌር ጦር መሣሪያ በፍጹም አይኖራትም” ሲሉ ዝተዋል።

ኔታንያሁ ከእስራኤሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ ቻናል 14 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በኢራን ጉዳይ ራሳችንን ከአቶሚክ ቦምቦች ታድገናል” ሲሉ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የተሰማው፣ በፓኪስታን አገናኝነት በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት በሥራ ላይ መዋል በጀመረበት ወቅት ነው።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም እና ያልተፈቱ ጉዳዮችን በንግግር ለመፍታት የሚያስችል ማዕቀፍን ያስቀምጣል።

እስራኤል ከቴህራን ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ያላትን ተቃውሞ በተደጋጋሚ የገለጸች ሲሆን፣ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት እንደምትሰነዝርም በተደጋጋሚ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...