ኬንያ በ2055 የአንደኛ ዓለም ሀገር ትሆናለች – ሩቶ

Date:

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኬንያን ከሦስተኛ አለም ወደ አንደኛ አለም ለማሸጋገር የ30 አመት ታላቅ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ሩቶ የረዥም ጊዜ ራዕያቸውን አስመልክተው ሲናገሩ፤ ኬንያ በትኩረት በማቀድና ተከታታይ ትግበራ በማድረግ፣ ፈጣን እድገት ያስመዘገቡት እንደ ደቡብ ኮሪያ፣ ሲንጋፖርና ቻይና ያሉ ሀገራትን አርአያ ትከተላለች ብለዋል፡፡

“ኬንያን ከሦስተኛ ዓለም ወደ አንደኛ ዓለም አገር ለማሳደግ 30 ዓመታትን ይወስድብናል – ልክ እንደ ኮሪያ፣ ሲንጋፖርና ቻይና። በ2055 ይህች ሀገር የአንደኛ ዓለም ሀገር ትሆናለች” ሲሉ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አስተዳደራቸው በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በኢንዱስትሪ ማስፋፋት፣ በትምህርት ማሻሻያና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሰረት እየጣለ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል – እኒህም በሚቀጥሉት አስርት አመታት ኬንያን የአለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ያደርጋታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...