ከሰሞኑ የተከሰተው የተለመደው የጉንፋን ዓይነት እንጂ አዲስ ወረርሽኝ አይደለም

Date:


ከሰሞኑ የተከሰተው የተለመደው የጉንፋን ዓይነት እንጂ አዲስ ወረርሽኝ አለመሆኑ በጥናት መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ከሰሞኑ የተከሰተው ጉንፋን በሰዎች ዘንድ ያለው የህመም ስሜት እና የወረርሽኙ በአጭር ጊዜ መዛመት አዲስ ወረርሽኝ መጥቶ ሊሆን ይችላል በሚል በተለያዩ ሰዎች ላይ ስጋት መፍጠሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ  በማዕከላዊ ኢንፍሉዌንዛ የምርምር ማዕከል በተደረገው ጥናት መሠረት ምንም ዓይነት አዲስ ወረርሽኝ ወይም በሽታ አለመገኘቱን ዋና ዳይሬክተሩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

ያም ሆኖ የክረምት ወራት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ በኢትዮጵያ የጉንፋን ወረርሽኝ ሊኖር ስለሚችል ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

በመሆኑም የመስከረም ወር መጨረሻ ላይ እንደመሆናችን መጠን፣ በቀጣይ ወራት የጉንፋን ወረርሽኙ የመተላለፍ መጠን እንዳይጨምር እና በህመሙ እንዳይጠቃ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና እና ከበሽታው ራሱን እንዲከላከል ለሕብረተሰቡ መልእክት ተላልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...