ለ30 ዓመታት አንድ እግራቸው አጥሮ የቆዩ አንድ ታካሚ እግራቸው ወደነበረበት መመለሱ ተነግሯል
ወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚሰጣቸው በርካታ የህክምና አገልግሎቶች መካከል የአጥንት ህክምና አገልግሎት ተጠቃሽ መሆኑ ተነግሯል። በዚህም በሚሰጠው የአጥንት ህክምና ክፍል አገልግሎት በርካታ ተስፋ ቆርጠው የነበሩ ታካሚዎች መፍትሄ እየሆነ መሆኑ ተገልጿል ።ታካሚዎች ባጋጠማቸው የተለያየ የእግር እንቅስቃሴ እክል ለዘመናት ሲቸገሩ መቆየታቸውን እና በሆስፒታሉ አገልግሎቱን እየተሰጠ መሆኑ ለበርካቶች ትልቅ እድል መሆኑን የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ መጀመሩ ተመልክቶ አገልግሎቱን ሰምተው ለህክምና ከአዲስ አበባ ድረስ የመጡ ታካሚዎች መኖራቸው ተገልጿል ። በእንዲሁም አንደኛው እግራቸው ከአንደኛው አጥሮ ለ30 ዓመታት የቆዩ አንድ ታካሚ በሆስፒታሉ ባገኙት ህክምና እግራቸው ወደነበረበት መመለሱን ተነግሯል።የወራቤ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከምስረታው ጀምሮ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ሕክምና ክፍል በርካታ የአጥንት መገጣጠሚያ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ያሉት በሆስፒታሉ የአጥንት ህክምና ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ኑረዲን ሀሚድ የህክምና ክፍሉ አገልግሎቱን በማስፋት ከቀላል እስከ ከባድ እና ዉስብስብ የአጥንት ስብራቶች ህክምና መስጠት መጀመሩብ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኑረዲን አክለው በተለይም ወራቤ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአጥንት ህክምና ክፍል የአገልግሎት በማስፋት የሙሉ ዳሌ አጥንት ቅየራ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አክለዋል። ይህ የህክምና አገልግሎት በአዲስ አበባ ውስጥ በውስን የጤና ተቋማት ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ አገልግሎቱ ሆስፒታሉ መጀመሩ የክልሉ እንዲሁም የአጎራባች የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው አገልግሎቱ የታካሚዎችን አቅም ባገነዘበ መልኩ እየሰጠ ይገኛል ተብሏል ።የቀዶ ህክምና አገልግሎት በጀመረ ጥቂት ወራት ውስጥም ወደ 14 ለሚሆኑ ታካሚዎች የተሳካ ቀዶ ህክምና መደረጉን አቶ አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ እና ተናግረዋል።
