ወታደራዊ ወጪዎች

Date:

በዓለም ላይ ወታደራዊ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
የዓለማችን ሀገራት በከፍተኛ ፍጥነት የጦር ኃይላቸውን እያስታጠቁ መሆኑን አንድ የጥናት ተቋም አስታወቀ።

እንደ ስቶክሆልም የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት (SIPRI ) ከሆነ በግጭቶች እና ጦርነቶች ምክንያት ወታደራዊ ወጪው በዓለም አቀፍ ደረጃ በ9.4 በመቶ ከፍ ብሏል። በአጠቃላይ የዓለም ሀገራት የጦር ኃይላቸውን ለማጠናከር 2,718 ቢሊዮን ዶላር ባለፈው የጎርጎሪዎስ ዓመት 2024 ወጪ ያደረጉ ሲሆን፤ ጭማሪው በሁሉም የዓለማችን አካባቢዎች ተስተውሏል።

በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ የጎላ የሚባል ነበር ተብሏል። ከዩናይትድ ስቴትስ ፣ቻይና ፣ሩሲያ እና ህንድ ቀጥሎ ለጦር ኃይላቸው ከፍተኛ መዋለ ነዋይ ካፈሰሱ አምስት ሀገራት መካከል ጀርመን አንዷ ሆናለች። ይህም ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የጀርመን ፌዴራላዊ መንግሥት ለመከላከያ ጦሩ 100 ቢሊዮን ዩሮ ለማዋል በመወሰኑ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና...