ለአማራ ክልል ዳኞች የተወሰነው የደመወዝ ጭማሪ በመዘግየቱ “ከፍተኛ ቅሬታ” ማስነሳቱ ተገለጸ

Date:

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ተፈጻሚ ሳይሆን በመዘግየቱ  “ከፍተኛ ቅሬታ” ማስነሳቱን ገለጸ።  ለደመወዝ ጭማሪው የሚያስፈልገውን በጀት የአማራ ክልል መንግስት እንዲመድብ ለማድረግ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “የቅርብ ክትትል እና ጥረት” እያደረገ መሆኑን ማህበሩ አስታውቋል። 

የዳኞች ማህበሩ ይህን ያስታወቀው ትላንት እሁድ ሚያዝያ 19፤ 2017 ለአባላቱ ባስተላለፈው መልዕክት ነው። ማህበሩ በዚሁ መልዕክቱ፤ ፍርድ ቤቶችን ከማጠናከር እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀመረውን የለውጥ ስራ የተሟላ ከማድረግ አኳያ የዳኞችን እና የጉባኤ ተሿሚዎችን ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻሉ “የማይተካ ሚና ያለው” “መሰረታዊ ነጥብ” እንደሆነ አስገንዝቧል።

የዳኞች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ለመመለስ፤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚቴ አዋቅሮ ጥናት ካደረገ በኋላ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ዐብይ ጉባኤ አማካኝነት ዝርዝር መመሪያ ማጽደቁን ማህበሩ አስታውሷል።

ዐብይ ጉባኤው ካጸደቀው የደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም በተጨማሪ ሀገር አቀፍ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ለሁሉም ሰራተኛ የተደረገ መሆኑን በትላንቱ መልዕክቱ የጠቀሰው ማህበሩ፤ ሁለቱም “እስካሁን ተፈጻሚ ባለመሆናቸው” በዳኞች ዘንድ “ከፍተኛ ቅሬታ” እያስነሳ መሆኑን ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...