ወይዘሪት ሜሮን ታደሰ የ2018 ዓ.ም. የ3ኛው “መሳላ አዋርድ” አሸናፊ ሆና መመረጧን “Visit Kambata” የተሰኘው ድርጅት አስታወቀ። ውድድሩ የተካሄደው የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነውን መሳላን ተከትሎ በዱራሜ ከተማ ነው።
ውድድሩ የተዘጋጀው “Visit Kambata” ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ነው። አሸናፊዋ ሚስ ሜሮን ታደሰ፣ ለሚቀጥለው አንድ ዓመት የከምባታን ባህል፣ ታሪክ እና የተፈጥሮ ጸጋዎች በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ኃላፊነት እንደተሰጣት አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የ2018 “ሚስ መሳላ” አሸናፊዋ ወ/ት ሜሮን ታደሰ በበኩሏ፣ ለድርጅቱ ላገኘችው እድል ምስጋናዋን አቅርባለች። “የብሔሩን ታሪክ፣ ባህልና የተፈጥሮ መስህቦችን በማስተዋወቅ ኃላፊነቴን እወጣለሁ” ስትልም ቃል ገብታለች።
የመሳላ አዋርድ የከምባታን ብሔር ልዩ የሆነውን የዘመን መለወጫ በዓል ከማድመቁም በላይ፣ ወጣቶች በባህላቸው ላይ እንዲኮሩ እና በማስተዋወቅ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ትልቅ መድረክ እየፈጠረ ይገኛል።
ከ
