ዓርብ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ

Date:

ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በመሆኑም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ

ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ሜክሲኮ፣

  • ከወሎ ሠፈር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ፣
  • ከቄራ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ ቡልጋሪያ፣
  • ከመርካቶ በአቡነ ተ/ኃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ የሚወስደው መንገድ አቡነ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ፣ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣
  • ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
  • ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣
  • ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣
  • ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣
  • ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
  • ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣
  • ከሐራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት፣
  • ከአዲሱ ገበያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮዲሮማ፣
  • ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ  ቤተ መንግስት አጠገብ፣
  • ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፣
  • ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ እንደሆነ ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ፦

  • በ011-1-26-43-59 ፣
  • በ011-5-52-63-02/03፣
  • በ011-5-52-40-77፣
  • በ011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ እንዲሰጥና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...