“ዘማይ ጉዞ” የተባለ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ

Date:

ኩባንያው ስራው የጀመረው በራሱ መኪኖችና አሽከርካሪዎች መሆኑን ተናግሯል።

በዚህም 1,680  የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ስራ እንዳሰማራቸው ተነግሯል።

“ዘማይ ጉዞ” ተሳፋሪዎች ንብረታቸውን ረስተው ቢወርዱ ለተሳፋሪው ጥቆማ የሚሰጥ ስርአት የተገጠመለት እንዳለው አስረድቷል።

ተሸከርካሪዎቹ የአደጋ ጊዜ ማሳወቂያ ሳይረን የተገጠመላቸው ስለሆኑ ተሳፋሪ ንብረቱን ጥሎ ቢወርድ እንኳን ሳይረኑ በመጮህ ለተሳፋሪው ጥቆማ ይሰጣል ፥ አሽከርካሪው የተሳፋሪው እቃ ውስጥ እንዳለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክር እንኳ መኪናው እንዳይንቀሳቀስ ሲስተሙ ይዘጋበታል ተብሏል፡፡

ዘማይ ጉዞ የራሱ የሆነ  የቻርጅ ጣቢያ፣ ዘመናዊ ጋራዥ እና  መኪና ማጠቢያ አገልግሎቶችን እንዳሟላም ተናግሯል።

ዘማይ ላኪ እና አስመጪ የግል ማህበር ዛሬ ወደ ስራ ካስጀመረው የሜትር ታክሲ የትራንስፖርት አገልግሎት ጎን ለጎን ዘመናዊ የክፍያ ስርዓት ወይም “ዘማይ ብር” የተሰኘ መተግበሪያም ይፋ አድርጓል።

ከጉዞ አገልግሎቱ ጋር ተያይዞ ክፍያዎችን ቀላል እና ፈጣን ለማድረግ ዘማይ ብር  መተግበሪያ ስራ ላይ ውሏል ተብሏል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...