የህንድ ትዕዛዝ ለፓኪስታን ዲፕሎማት

Date:

ህንድ  የፓኪስታን ዲፕሎማት በ24 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ በኒው ደልሂ  የፓኪስታን ኤምባሲ ዲፕሎማት’’ ያልተገባ ነገር አደርጓል’’ በሚል የህንድ የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሷል።

ከአንድ የኤምባሲ ሰራተኛ የማይጠበቅ በሚል ክሱን ለማጠናከርም ሞክሯል ሚኒስቴሩ።

ያልተገባ ነገር አድርጓል ከማለት የተሻገረ  ተጨባጭ ሀሳብ ከደልሂ በኩል ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋ አልሆነም።

ፓኪስታን እና ህንድ አምስተኛውን ጦርነታቸውን ሊያደርጉ ነው በሚል ቀጠናው ስጋት ውስጥ ባለበት ሰዓት ባለስልጣኑን ማባረር ተጨማሪ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ተብሏል።

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አሸባሪዎችን እና ስጋት የደቀኑብንን ሁሉ መምታታችንን እንቀጥላለን ካሉ በኋላ ነው  የዲፕሎማቱ ይውጣ መግለጫ ይፋ የሆነው።

በሌላ በኩል ፓኪስታን ተኩስ አቁሙን ለማክበር ቁርጠኛ መሆኗን በመግለጽ ከኒው ድለሂ በኩል ጥቃት ከተሰነዘረብኝ ግን አደገኛውን አጸፋ እሰጣለሁ በሚልም ዝታለች።

የኒው ደልሂን ውሳኔ እስላማባድ ከጦርነቱ ጋር ልታገናኘው ትችላለች የሚል ስጋትም ተደቅኗል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ አገራት መካከል ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት በተኩስ አቁም ለጊዜውም ቢሆን ማስቆማቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አደይ ኢትዮጵያ ጓል አስመራ…!!

የቀድሞ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የስንብት ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ...

ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር...

በ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደለት

ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው...

ክፍሌ አቦቸር እና ‹‹ይህ ነው ምኞቴ…››

ሠሎሞን ለማ ገመቹ ግዮን መጽሔት :- ሻለቃ ከፍሌ አቦቸር ስለ...