የህወሓት ታጣቂዎች ክፍፍል ወደ ግጭት እንዳያመራ

Date:

የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ እርስ በርስ ግጭት ሊያመሩ ነዉ የሚል ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው «ሳልሳይ ወያነ ትግራይ» አሳሰበ።

ሊፈጠር የሚችለዉን ቀውስ ለማስቀረትም በትግራይ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።


የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ መኮንኖች ባለፈው ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም «ለአንዱ የህወሓት ክንፍ ያጋደለ» የተባለለትን የአቋም መግለጫ በማንፀባረቃቸው፣ በትግራይ ሐይሎች መካከል መከፋፈሎች መፈጠራቸው ይነሳል።

ይህ ደግሞ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች ያሉበት ሌላ ታጣቂ ሐይል እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ለወራት የቆየው ይህ አዲስ ሐይል ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አዲሱ ታይል እዚያዉ ትግራይ ከሚገኘዉ ነባሩ ኃይል ጋር የእርስ በርስ ግጭት እንዳይገጥም የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ ተፈጥሯል ሲል ሚልዮን ሃይለስላሴ ከመቐለ ዘግቦልናል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...