ሰከላ የተሰኘና በትምህርት ሚኒስቴር ስርአተ ትምህርት መሰረት እስከ12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም መጽሐፍትና አጋዥ ማጣቀሻዎችን በተንቀሳቃሽ ምስል እና በድምጽ የሚያካትት የቴክኖሎጂ ስርዓት ወደ ስራ ገብቷል።
ቴክኖሎጂው የትምህርት አስተዳደርና አካዳሚክ ስራዎችን፣ የወላጆችና የትምህርት ቤት እንዲሁም የተማሪና አስተማሪ ግንኙነትን ለማሳለጥ እንደሚረዳ ተገልጿል።
‘ሲስተሙ’ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የበለጸገና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መጠቀም የሚያስችል ነው።
ማንኛውም የትምህርት ተቋምም በsekela.appዌብሳይት ላይ በመመዝገብና መረጃን በማስገባት በጥቂት ቀናት ውስጥ ተቋሙን ማዘመን እንደሚችል ተመላክቷል።
የሰከላ ‘ሲስተም’ ከገጠር እስከ ከተማ ያሉትን ትምህርት ቤቶች በኔትዎርክ በማገናኘት ሀገራዊ መረጃን በመሰብሰብ ተዓማኒነት ያለው ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ጭምር እንደሆነ ሰምተናል።
የቴሌኮም አገልግሎትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎችና በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት ለተቋረጠባቸው ቦታዎች የሚያደርጉትን ጥረት ይህ ‘ሲስተም’ የሚያግዝ በመሆኑም በጋራ መግባባት መስራት እንደሚቻል ተገልጿል።
