የመዲናዋ የመሬት ልማት 11 አመራርና ሰራተኞች በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቀድሞ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራር እና ሰራተኞች በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

  1. አቶ ሞሊቶ አባይነህ ኤርቃሎ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀድሞ ም/ኃላፊ
  2. ኢ/ር ቸርነት አበበ የአደቴ፦ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የቀድሞ ኃላፊ
  3. ሰለሞን በላይ መኮንን፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቴክኒክ ጉዳይ ወሳኝ ባለሙያ
  4. አድማሱ አዳነ ወንድሙ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቅሬታ እና አቤቱታ ባለሙያ
  5. ግዛቸው ሙሉጌታ ደሴ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ
  6. ደረጀ ጎሹ ሀይሌ፡-የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
  7. አለምፀሃይ ለማ ኪ/ማርያም፡- የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 መሬት ልማትና አስተዳደር የሰነድ አጣሪ ባለሙያ
  8. ግርማ ተፈራ አያና፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህግ/ቴክኒክ ጉዳይ ክትትል ዳይሬክተር
  9. አማኑኤል አለማየሁ ማሞ፡- የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ
  10. ቢኒያም ሀይሉ ገብሬ፡- የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ
  11. አቢዮት ጁፋሬ ባይሳ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው በፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆ ምርመራው ቀጥሏል።

ግለሰቦቹ ከግበረ አበሮቻቸው ጋር በጥቅም ተመሳጥረው በህዝብና በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያለአግባብ በመጠቀም ተጠርጥረዋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው አየር መንገድ አከባቢ የህዝብ እና የመንግስት ይዞታ የሆነውን በ9ኛው መዋቅራዊ ፕላን በዓድዋ ፓርክነት ተይዞ የነበረውን እና በ10ኛ መዋቅራዊ ፕላን በዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ልዩ ልዩ የከተማው መተንፈሻ አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት በከተማ ደረጃ በመናፈሻነት ለህዝብ አገልግሎት የተያዘ እና በመሬት ባንክ ውስጥ ያለን ይዞታ ያለ ህጋዊ ምክንያት ሰነድ አልባ ይዞታ ነው

በማለት ለዮርዳኖስ ፤ ዘውዲቱ እና ጓደኞቻቸው የሲሚንቶ አከፋፋይ ህብረት ሽርክና ማህበር ለሚባሉት የቦታው ስፋት 2 ሺህ 905 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የቦታው ሊዝ ዋጋ 168 ሚሊየን 724 ሺህ 405 ብር የሚገመትን ጉዳት በማድረስ ከወረዳ ፤ ክ/ከተማ እና መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ድረስ በጥቅም ተሳስረው ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል።

በዚህም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ምርመራው ቀጥሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...