ሩሲያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በሚሳኤሎች በመታገዝ በኪዬቭ ላይ ጥቃት ፈጸመች፡፡
ሩሲያ 550 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን የተጠቀመች ሲሆን ከነዚም መካከል 11 ሚሳኤሎችን እና ሻሂድ ድሮኖች እንደሚገኙበት የሀገሪቱ አየር ሃይል አስታውልቋል። የአየር ላይ ጥቃቱን ተከትሎ የፍንዳታ እና የተኩስ ድምጾች ተሰምተዋል።
የኪየቭ ከንቲባ እንደተናገሩትም ቢያንስ 23 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 14ቱ ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል እንዲሁም የጥቃቱ ዋና ኢላማ ኪየቭ ነበረች ብለዋል፡፡
የዩክሬን አየር መከላከያዎች ሁለት ሚሳኤሎችን ጨምሮ 270 ኢላማዎችን ማምከን መቻሉ እየተነገረ ይገኛል፡፡
ጥቃቱ የደረሰው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በመገናኘት አስተዳደራቸው አንዳንድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን ለማቆም ባደረገው ውሳኔ ላይ የመጀመሪያውን የህዝብ አስተያየት ከሰጡ ከሰዓታት በኋላ ነው።
