የሚድሮክ ሰባት የሻይ ቅጠል ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች

Date:

የሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ እንደገለጹት የግሉ ዘርፍ  የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው ፡፡

ሚድሮክ በጅማና በኢሉባቦር አራት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አንድ ሺህ አርሶ አደሮችን አደራጅቶ ከፍተኛ የሻይ ቅጠል ምርት እያመረተ ይገኛል። ከሚመረተው ምርት 20 በመቶ ለውጭ ገበያ ያቀርባል ሲሉ አቶ ጀማል ገልጸዋል ፡፡

ነገር ግን በአካባቢው ከ150 ሺህ አርሶ አደሮች በላይ በቆሎ እያመረቱ በትንሽ ገቢ በድህነት እየኖሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ጀማል፤ የሻይ ምርትን ለማሳደግና ገቢን ለመጨመር የኦሮሚያ ክልል በ30 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሻይ ምርት ለማምረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ሚድሮክ የሙያ እገዛ፣ የችግኝ አቅርቦት እና ሌሎች ቴክኒካል ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ጀማል፤ ሚድሮክ ከእርሻ መሬቱ በ20 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ሰባት ግዙፍ የሻይ ቅጠል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ቢያንስ ከ40 ሺህ በላይ ሻይ ቅጠል አምራቾችን ማፍራት እንደሚቻል መናገራቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...