የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ ሰጠ

Date:

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ሰበብ በማድረግ፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወይም ከሌሎች የመንግሥት ተቋማት ውክልና አለን የሚሉ ሕገ-ወጥ አካላት መበራከታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ አጭበርባሪዎች በግል ስልክ፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፣ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ገንዘብ በመጠየቅ ዜጎችን እያጭበረበሩ መሆኑን ነው የጠቆመው።

ሚኒስቴሩ ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አገልግሎት በማንኛውም የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ወይም በስልክ ጥሪ በፍጹም ገንዘብ እንደማይጠይቅ አረጋግጧል።

​ማንኛውም ሰው የመንግሥት ተቋምን በመወከል በዲጂታል መንገዶች የገንዘብ ጥያቄ ሲያቀርብ፣ የግል ወይም የባንክ መረጃዎችን (የባንክ ሂሳብ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል ወይም የOTP ሚስጥራዊ ኮድ) አሳልፎ ከመስጠት መቆጠብ እንደሚገባው ጠቁሟል።

ዜጎች እንዲህ ዓይነት አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥሙ መረጃውን ወዲያውኑ በአቅራቢያ ለሚገኙ የሕግ አስከባሪ አካላት ወይም ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መዋቅሮች በአስቸኳይ እንዲያሳውቁም ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...