የሩሲያ ሙዚየም አፍሪካ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ኤግዚቢሽን ሊያዘጋጅ ነው

Date:

የሞስኮው ፑሽኪን ስቴት የሥነ ጥበባት ሙዚየም ዳይሬክተር ኦልጋ ጋላክቲኖቫ አፍሪካ “ፍላጎት እና ሰኬትን መሳቧን የቀጠለች ትልቅ የባህል አድማስ
ነች” ብለዋል።

የአፍሪካ ባህል በሩሲያ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ቢሆንም አሁንም ብዙ የማይታወቁ ገጽታዎች እንዳሉት ጋላክቲዮኖቫ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።

በተለይም ብዙም የማይታወቀው የዘመናዊ አፍሪካ ጥበብ ሊታይ እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የሙዚየሙ ዳይሬክተር አክለውም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተሠሩ ፕሮጀክቶች እንደሌሉ የገለፁ ሲሆን ሆኖም አሁን ላይ ለውጦች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እ.አ.አ በ1912 የተመሠረተው እና ወደ 700 ሺህ የሚጠጉ ሥራዎችን የያዘው የፑሽኪን ሙዚየም በየዓመቱ እስከ 1.3 ሚሊዮን ጎብኚዎችን በመሳብ በሩሲያ በብዛት ከሚጎበኙ ሙዚየሞች አንዱ ነው።

@sputnik_ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...