የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ያለን አካባቢ መቆጣጠሩ ተነገረ

Date:

የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በብሉ ናይል ግዛት የምትገኘውን የአል ሲልክ አካባቢን ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መቆጣጠሩን ገልጿል።

የሱዳን ጦር አካባቢውን ለመቆጣጠር በተደረገው ውጊያ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተዋጊዎችና በአጋሩ የሱዳን ህዝብ የነፃነት እንቅስቃሴ በሰሜን ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሷል ብሏል።

የሱዳን ህዝብ የነፃነት እንቅስቃሴ በሰሜን የደቡብ ኮርዶፋንና ብሉ ናይል አካባቢዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ ከ2011 ጀምሮ እየተዋጋ ያለ ነው።

በተያያዘ ዜና የሱዳን ጦር ለሁለት አመት ያህል በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ስር የነበረችውን ሌላኛዋን የኮርዶፋን ከተማ አል ዳላንጅን የያዘ ሲሆን፣ ውጊያዎች በኮርዶፋን ተባብሰው ቀጥለዋል ተብሏል።

ዘገባው የአናዶሉና ሮይተርስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...