የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከካርቱም ለቆ መውጣቱን አመነ

Date:

ዳጋሎ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “በርግጥም ከካርቱም ለቀን መውጣታችንን አረጋግጣለሁ፤ ነገር ግን በጠንካራ ቁርጠኝነት እንመለሳለን” ብለዋል።

ሔሚቲ በሚል ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ዳጋሎ በቴሌግራም በተሰራጨ የተቀዳ ድምጽ ብሔራዊ ጦሩ ካርቱምን በመቆጣጠሩ የየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለቆ መውጣቱን አረጋግጠዋል።

ዳጋሎ በዚሁ መግለጫቸው “ባለፉት ጥቂት ቀናት ካርቱምን ለቀን ወደ ኦምድርማን ለመውጣት ተገደናል።

ይህም በአመራሩ የተወሰደ ስልታዊ እና የተቀናጀ ዉሳኔ ነበር” ብለዋል ኃይላቸው የበለጠ ተጠናክሮ እና በሸናፊነት ወደ ካርቱም እንደሚመለስ በማመልከት ።

እንደዚያም ሆኖ ግን የብሄራዊ ጦር ይዞታውን እያጠናከረ ወደ ኦምዱርማን የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሎ በማዕከላዊ የከተማዋ ክፍል እየደረሰ እንደሚገኝ  ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የብሄራዊ ጦሩ አዛዥ ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ትናንት ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ ከአር ኤስ ኤፍ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር ግልጽ አድርገዋል።

መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...