የስምረት ስራ አስፈጻሚ ከኃላፊነት ተነሱ

Date:

የስምረት ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚዋ በትግራይ ከነበራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል።

ሃላፊዋ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከነበራቸው የስራ ሃላፊነት የተነሱት ፓርቲያቸው ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አድርጎ ከመረጣቸው በኋላ እንደሆነ ተረጋግጧል።

የየኢንዳስትሪ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አልማዝ ገብረፃዲቕ ደውሎ አስተያየታቸው ለማካተተ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

ከትግራይ ጦርነት በፊት ጀምሮ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እስከ ተፈጠረው መለያያት ድረስ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ሃላፊዋ አሁን ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ በፊት የክልሉ የከተማና የኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ወደ ስልጣን ከመጡበት ማግስት ጀምሮ ሲመሩት የነበረው የከተማና የኮንስትራክሽን ቢሮ ከአቶ ጌታቸው በኃላ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አማኒኤል አሰፋ እንዲተኩት ሆኗል።

ከ6 ወር በኃላ ደግሞ ከተሰጣቸው አዲሰ የቢሮ ሃላፊነት እንዲሻሩ ሆኗል።

ቲህቫህ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...