የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ አዲስ አበባ

Date:

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመምከር በሚቀጥሉት ቀናት በአዲስ አበባ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጉብኝቱ በአፍሪካ ቀንድ የተፈጠረውን ውጥረት በውይይት ለመፍታት ያለመ ሲሆን፣ በሁለቱ መሪዎች ውይይት ላይ ሦስት ወሳኝ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

ዘገባዎቹ እንዳመለከቱት፣


ከመሪዎቹ የውይይት አጀንዳዎች አንዱ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን ውዝግብ በሽምግልና ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይችላል። ይህ የሶማሊያ መንግስት በቀጠናው ሰላም ለማስፈን ገንቢ ሚና ለመጫወት ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ሁለተኛው እና ዋነኛው የውይይት ነጥብ ደግሞ በሶማሊያ ውስጥ ስለሚገኙት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁኔታ የሚመለከት ነው። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ፣ በተለይም ከአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል (ATMIS) ውጪ በሀገሪቱ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ጉዳይ አንስተው እንደሚወያዩ ተገልጿል።

የፕሬዝዳንቱ አቋም፣ እነዚህ ወታደሮች ወደ አለም አቀፍ እውቅና ባለው የሰላም ማስከበር ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተቱ ወይም ሁኔታቸው በግልጽ እንዲታወቅ ማድረግ እንደሆነ ዘገባዎቹ ጠቁመዋል።

ይህ ጉብኝት በቀጠናው ያሉትን ፖለቲካዊ እና ጸጥታዊ ጉዳዮች በጋራ ለመገምገም እና የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተዘግቧል።

(via Zehabesha)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...