ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማ ሀምሌ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ሊያካሄድ ባቀደው የሺህ የባለትዳሮች የጋብቻ አመታዊ ክብረ- በዓል ላይ አንጋፋ በትዳር ህይወት ረዥም አመታትን የኖሩና በመልካም ትዳር ዓርዓያነታቸው የሚመረጡ እድሜ ጠገብ አምስት ባለትዳሮችን የሚሸልም መሆኑን እንዲሁም የጋብቻ አመታዊ ክብረ በዓላቸውን ለማክበር ምዝገባ ካካሄዱ ጥንዶች መካከል ለ80 አመታት በጋብቻ የኖሩ ባለትዳር ጥንዶችን አስተዋውቋል
ያሜንት ሃ/የተ/የግል/ ማህበር በ2017 ዓ.ም ለ500 ኢትዮጵያውያን ጥንዶች የጋብቻ ቀናቸውን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ ሲሆን ይኸውም የ10፣ 15፣ 25፣50 እና ከዚያም በላይ ጊዜ የቆዩ ባለትዳሮችን ያካትታል ተብሏል፡፡
ሀምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ልዩ ልዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ከተጋቡ ረጅም ዘመናት ያስቆጠሩ 20 ጥንዶች መሳጭና ትምህርት ሰጭ የሆኑ የህይወት ተሞከሮዎቻቸውን በሁነቱ ለታደሙና በሚዲያ ለሚከታተሉ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲያደርሱ ይመቻቻል።
በሀምሌ ወር 2017 ዓ.ም ሁለት የምክክር መድረኮችን (ወርክሾፖች) በማዘጋጀት በጋብቻ በተሳሰሩ ጥንዶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው መሠረታዊ የተግባቦት ሥርዓት በተለይም በባለትዳሮች መካከል ግጭትና አለመግባባት ስለሚፈታበት ሁኔታ እንዲሁም የማህበረሰብን ትስስር ማጎልበት በሚቻልበት ዙርያ በምሁራንና ልምድ ባካበቱ ጥንዶች የታገዘ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ለ50 ዓመትና ከዚያ በላይ ትዳራቸውን በስኬት የመሩ 3ጥንዶችን የጋብቻ ህይወት ተሞክሮ በመገናኛ ብዙሃን (በምስል/በፎቶ አውደርዕይ፣ በምስል በድምጽ/በቪዲዮ፣ በልዩ ልዩ ብዙሃን መገናኛ መንገዶች) አማካኝነት የህይወት ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ ህብረተሰቡን ማስተማር፣ በጋብቻ ህይወት ለረጅም ዘመናት በፍቅርና በመከባበር የኖሩ የ5 ጥንዶችን ልምድ በመጽሄት፣ በምስልወድምጽ/በቪዲዮ፣ በድረገጽ መጣጥፎች ይቀርባሉ።
(በድሬ ትዩብ)
