የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ኮከብና አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

Date:

ፊርማው በማኖር የማይረሳ መታሰቢያ አበርክቶለታል

የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንና የአርሰናል እግር ኳስ ኮከብ ባካሪ ሳኛ በኢትዮጵያ እያደረገ ባለው ቆይታ፣ ከታላቁ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ጋር በኃይሌ ግራንድ አዲስ ሆቴል ተገናኝቷል።

ሁለቱ ስፖርተኞች በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ቡና አብረው ከመጠጣታቸው ባለፈ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ለብዙ ምዕራባውያን የዓለም ስፖርተኞች ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴን ማግኘት እንደ ትልቅ ዕድልና ክብር የሚቆጠር ሲሆን፤ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴም ለባካሪ ሳኛ የራሱን ፊርማ (Autograph) በማኖር የማይረሳ መታሰቢያ አበርክቶለታል።

ይህም ጀግናው አትሌታችን ኃይሌ ገ/ሥላሴ በዓለም መድረክ ያለውን የላቀ ቦታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ክስተት ነው፡፡

Haile Hotels and Resorts

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...