በወጣቱ ሠዓሊ ብርሃኑ ማናዬ የተዘጋጁ ሥዕሎች የቀረቡበት”የተሸመኑ ትውስታዎች” የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 2 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖስት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ”The Space Ethiopia” የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
በዳግም አበበ አጋፋሪነት የተዘጋጀው ይህ አዉደርዕይ የተለያዩ የስዕል አቀራረቦችን እንዲሁም በተለያዩ የአሳሳል ዘይቤ የተሰሩ የስዕል አይነቶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።አውደርዕዩ እስከ ሰኔ 18 2017 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
