የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2025 በሚል የተካሄደው ሦስተኛው የኢንቨስትመንት ፎረም የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል ።
ኮሚሽኑ ከአምስት አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር 1 ነጥብ 6 ቢልየን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ኢንቨስትመንት ሥምምነት የተፈራረመ ሲሆን ኩባንያዎቹም በማእድንና በሀይል ዘርፍ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሰማሩ እንደሆነ ተገልጿል ።
