የታላቁ ምሁር መታሰቢያ በድምቀት ተካሄደ

Date:

የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አዳራሽ ተካሄዷል።

በፕሮግራሙ ላይ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ ባልደረቦች፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የክራር ጨዋታ፣ መነባንብ እና የዶ/ር ደረጄን አስተማሪነት፣ የህግ እውቀትና የምርምር ስራዎች የሚዘክሩ ልዩ ልዩ ዲስኩሮች ቀርበዋል።

እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኘው “ዶ/ር ደረጄ መታሰቢያ አፀደ ህፃናትና ቤተመጽሐፍ” ግብአት የሚሆኑ መጻሕፍት እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ተሰብስበዋል።

አዘጋጆቹ መታሰቢያው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው የህግ ክፍል መምህራን እና ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር በህግ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ተማሪዎች የገንዘብ እገዛና የውድድር ድጋፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኩላሊት እጥበት ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል ጥናት ተዘጋጀ

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኩላሊት ህመም ስርጭት...

ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የ‘ሴሬብራል ፓልሲ’ ቀን የእግር ጉዞ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የ‘ሴሬብራል ፓልሲ’ ቀንን...

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...