የትግራይ ህክምና ማህበር የዶ/ር የማነ ገብረማርያምን መታሰር አወገዘ

Date:

የትግራይ ህክምና ማህበር (TMA) የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የአዲግራት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር የማነ ገብረማርያም ያለአግባብ መታሰራቸውን በመግለጽ ድርጊቱን ተቃውሞ መግለጫ አወጣ።

ማህበሩ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ዶ/ር የማነ በትግራይ የህክምና እና የትምህርት ማህበረሰብ ዘንድ በጤና አገልግሎት አመራርና በህክምና መምህርነታቸው የሚታወቁ አንጋፋ ባለሙያ መሆናቸውን ገልጿል።

በተጨማሪም የህክምና ማህበሩ የቀድሞ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል እና በአሁኑ ወቅት የአማካሪ ቦርድ አባል ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክቷል።

እንደ ማህበሩ መረጃ ከሆነ፣ ዶ/ር የማነ በቁጥጥር ስር የዋሉት “MedEd Africa” በተሰኘ የሙያ ትምህርት መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ ነው።

እስካሁንም ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸውም ሆነ ለማህበሩ የታሰሩበት ህጋዊ ምክንያት እንዳልተገለጸ ማህበሩ አሳውቋል።

የህክምና ማህበሩ ይህ እስር የህክምና ባለሙያዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት እና ሙያዊ የሳይንስና የትምህርት ተግባራትን ያለ ምንም ትንኮሳ የማከናወን መብታቸውን የሚጥስ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጊቱ በትግራይ ክልል እያገገመ የሚገኘውን የጤና ስርዓት፣ በተለይም ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ የሚያገለግለውን ሆስፒታልና የቀጣይ የጤና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥነውን የትምህርት ማዕከል ስራ የሚያደናቅፍ ነው ብሏል።

ማህበሩ በመግለጫው

• ዶ/ር የማነ ገብረማርያም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ።

• በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት በግልጽ እንዲታወቅና የህግ የበላይነት እንዲከበር እንዲሁም

• የጤና እና የአካዳሚክ ህክምና አመራሮች ደህንነትና ገለልተኝነት እንዲከበር ጥሪ አቅርቧል።

የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ዓለም አቀፍ የጤና አጋሮች የዶ/ር የማነን መፈታት እንዲያረጋግጡና የህክምና ባለሙያዎች ያለ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ ግፊት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...