2ኛው የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

Date:

“የአፍሪካን የጤና ባለሙያዎች ኃይል ለመጪው ግዜያት ማዘጋጀት፦ አጋርነትን፣ ቴክኖሎጂን፣ ፈጠራን እና አመራርን መጠቀም” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤው በአኅጉሪቱ የሕክምና ትምህርትን ለማሳደግ እና የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማጠናከር ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ቤቶች ጥምረት እና ከግሎባል ሄልዝ ኢክዊቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ  ጉባኤ ለወደፊት ፈተናዎች ዝግጁ የሆነ የጤና ባለሙያ ኃይል ለመገንባት፣ በአፍሪካውያን የሚመሩ የፈጠራ መፍትሔዎችን ማሳደግ ላይ ያተኩራል ተብሏል።

የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ (ሜድኤድአፍሪካ 2026) በአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር በተግባራዊነት፣ በፈጠራ እና በስትራቴጂካዊ አጋርነቶች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ መገለፁን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

👉 ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ46 ሀገራት እና ከ117 ተቋማት የተውጣጡ ከ750 በላይ ባለድርሻአካላት እየተካፈሉ ሲሆን፤ ይህም በአኅጉሪቱ በሕክምና ትምህርት ዘርፍ ከተደረጉ ትላልቅ ስብሰባዎች አንዱ ያደርገዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...