የናይጄሪያ መንግስት ለትራምፕ ወታደራዊ እርምጃና ዛቻ ምላሽ ሰጠ

Date:

የትራምፕ አስተዳደር በናይጄሪያ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ማቀዱን እና ሀገሪቱን ለሃይማኖት ነፃነት ‹‹ልዩ ስጋት ያለባት ሀገር›› በማለት መሰየሙ ከናይጄሪያ መንግስት ከፍተኛ ተቃውሞ አስከትሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ክርስትና በናይጄሪያ ስጋት ተጋርጦበታል በማለት የመከላከያ ሚኒስቴር ለወታደራዊ እርምጃ እንዲዘጋጅ አዘዋል፡፡

የአገሪቱ መንግሥት በፍጥነት እርምጃ የማይወስድ ከሆነ፤ ለናይጄሪያ የሚሰጠውን እርዳታ እና ድጋፍ ወዲያውኑ እናቆማለን ሲሉ ዝተዋል።

በምላሹም የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ፤ ይህ ገለጻ ብሄራዊውን እውነታ አያንጸባርቅም ብለዋል፤ የሃይማኖት ነፃነት እና መቻቻል የጋራ ማንነታችን ዋና አካል ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም ናይጄሪያን በ2020 በተመሳሳይ ዝርዝር ውስጥ አስገብታት የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ስያሜ በ2023 ተነስቷል።

የናይጄሪያ የጸጥታ ቀውስ ብዙ ገጽታ ያለው ሲሆን፣ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን፣ የአርብቶ አደር ግጭቶችን እና መገንጠል የሚሹ ቡድኖችን ያጠቃልላል።

በክርስትያኖች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አለም አቀፍ ትኩረት የሳቡ ቢሆንም፤ ተንታኞች እንደሚሉት የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሚበዙበት በሰሜኑ ክፍል ግን አብዛኞቹ ተጎጂዎች ሙስሊሞች ናቸው።

የሀገሪቱ 2መቶ20 ሚሊየን ህዝብ በክርስትና እና በእስልምና እኩል የተከፋፈለ በመሆኑ ስለ አንድ ወገን የሃይማኖት ስደት የሚነገሩ ትርክቶችን ተቀባይነት እንዳይኖራቸዉ ያደርጋል፡፡

የአሜሪካ ዕርምጃ በናይጄሪያ ውስጥ ክርክርን አስነስቷል። አንዳንዶች እንደ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሲመለከቱት፤ ሌሎች ደግሞ ሊኖሩ የሚችሉ ጥቅሞች አሉ ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት የምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ በክርስትያኖች ላይ የሚደርሰውን ግድያ ማስቆም ካልቻለች መከላከያ ፈጣን የሆነ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላት እና ነዳጅ አምራች ለሆነችው ናይጄሪያ የአሜሪካ መንግሥት የሚሰጠውን እርዳታ እና ድጋፍ ወዲያውኑ እንደሚያቆም በትሩዝ ሶሻል ልጥፋቸው ላይ ገልፀዋል።

አሜሪካ ወታደሮቿን የምትልክ ከሆነ አሸባሪዎችን ጠራርጎ ለማስወገድ ይሆናል ያሉት ትራምፕ፤ በናይጄሪያ ክርስትያኖች ላይ ይደርሳል ስላሉት ግድያ እና ስቃይ ግን ተጨባጭ መረጃ አልሰጡም ሲል የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ክፍሌ አቦቸር እና ‹‹ይህ ነው ምኞቴ…››

ሠሎሞን ለማ ገመቹ ግዮን መጽሔት :- ሻለቃ ከፍሌ አቦቸር ስለ...

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...