የአመራር ሽኝትና አቀባበል መርሐ-ግብር ተከናወነ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን  የቀድሞ አመራሮችን የመሸኘትና አዲስ የተሾሙ ዋና ሥራ አስኪያጅን የመቀበል መርሐ-ግብር አካሄዷል።

በቅርቡ በተደረገው የአመራር ሽግሽግ መሠረት ተቋሙን በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ ለቆዩት ለአቶ ዲዳ ድሪባ እና በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ለአቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ አዲሱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር እሸቱ ለማ የቀድሞ አመራሮች ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር በመቀናጀት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን ውጤታማ ለማድረግ ያከናወኗቸውን ተግባራት አውስተው፣ በቀጣይም ተቋሙን በዕውቀታቸውና በልምዳቸው እንደሚያግዙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ተሸኚ አመራሮቹ በበኩላቸው በቆይታቸው ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና በማቅረብ፣ ለዶ/ር እሸቱ ለማ መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል።

ፕሮግራሙ አመራሮቹ በቀጣይ የሥራ ምድባቸው ለተቋሙ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በገለጹበት የወንድማማችነት መንፈስ ተጠናቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...