የአማርኛ ፊደላት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀረቡ

Date:

ብሔራዊ ፊደልን የብሔር ብሔረሰቦች የትምህርት መገልገያ መሣሪያ እንዲሆን የኢትዮጲያ ማህበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጠየቀ

የኢትዮጲያ ማህበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት(Ethiopian social partnership Advocacy) በኢትዮጲያ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በሴቶች በወጣቶች እንዲሁም በተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች የሚያስፈልጋቸውን አነቃቂ ስልጠናዎች በማዘጋጀት ተደራሽ ያልሆኑ የማህበረሰቡ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በቀን 2/10/2017 ባወጣው መግለጫ ብሔራዊ ፊደልን የብሔር ብሔረሰቦች የትምህርት መገልገያ መሣሪያ እንዲሆን የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጠይቋል።

የመግለጫው አላማም ኢትዮጲያ ያልዋትን የተለያዩ ጥንታዊ ታሪኮቿን እና ቅርሶቿን ወጣቱ ትውልድ እና ሁሉም የማህበረሰቡ ክፍሎች በሚገባ እንዲያውቅ እና ጠብቆ እንዲያስቀጥል የሚያስችል ስራ እንዲሰራ የሚያደርግ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል።

የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል

ጉዳዩ፦ ብሔራዊ ፊደልን የብሔር ብሔረሰቦች የትምህርት መገልገያ መሣሪያ እንዲሆን መጠየቅን ይመለከታል፡፡

ጥንታዊት፣ ታላቅና ገናና ስም ያላት ኢትዮጵያ አገራችን በዘመናት የትውልዶች ቅብብሎሽ ባፈራችውና ለዓለም ባበረከተችው ሥልጣኔ፣እንዲሁም በመንፈሳዊና ቁሳዊ ሃብትና ፀጋዋ ትታወቃለች። ሆኖም ግን

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ መሪ ራስ ናት ተብላ ከብዙዎች አድናቆትን ስታተርፍ ይህንን እውነታ ከፍ አድርጎ ለማሳየት በቂ ሥራ ባለመሠራቱ አንዳንድ ዜጎች ይህንን ሐቅ ጥያቄ ውስጥ ሲያስገቡት ይስተዋላል።

በተለይም ወጣቱ ትውልድ፤ አገራችን ኢትዮጵያ ያለባትን ዘርፈ ብዙ ችግር በማየት፣ የማይካደውን ገናና የአገሩን ታሪክና ስም ለመቀበል ሲያዳግተው ይታያል።

ይሁን እንጂ ከአባቶቹ የተረከባትን ጥንታዊትና ገናና የታሪክ፣ የባህል፣ የሥልጣኔ፣ የሃይማኖት፣ የጥበብ መገኛ የሆነች ተወዳጅና መተኪያ የሌላት አገሩን ይወዳታል።

በተጨማሪም፤ የነገውን ተስፋና ሕይወት በትግልና በመሥዋዕትነት ለመገንባትና ለማነፅ፣ ወደፊቱን በእጁ ለመሥራት ዕድሉን አሁን አግኝቷል ፡፡

ስለሆነም ትውልዱ አገራችንን ወደ ነበረችበት ከፍታ ለመመለስ፣ በሕዝቦችዋ ጥረትና ድካም የተገነባውን ህብረ-ብሔራዊ እና ዘመን አይሽሬ የሆነውን ታሪክና መልኳን ለማፍካት ታጥቆ መነሳት አለበት ።

ለዚህአፅንኦት በመስጠት አበው ቀለም በጥብጠው፣ ብራን ፍቀው የከተቧቸው ድርሳናትን፤ እንዲሁም የባህርማዶ የታሪክ ሊቃውንት፣ በየመካነ አእምሮ የሰነዷቸውን የምርምር ሥራዎችን፣ ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

የቅርሶቻችንን እና የታሪካችንን ጠቀሜታ በውል የተገነዘቡት ሌሎች ሀገሮች፣ የኛን ጥንታዊ ቋንቋዎችም ሆኑ ፊደላት በታላላቅ የምርምር ተቋሞቻቸው ውስጥ እንዲጠኑ ሁኔታዎችን አመቻችተዋል።

ይህንንም ገቢራዊ ለማድረግ ያነሳሳቸው፤ በጥንታዊ ድርሳናት ውስጥ ትኩረት ተነፍጓቸው የኖሩት ጥበቦች እና ዕውቀቶች በተግባር ቢመነዘሩ፤ የሚያበረክቱትን ዘርፈ – ብዙ ፋይዳ ቀድመው ማየት በመቻላቸው ነው።

እነዚህ ቅርሶች፣ የትላንት ታሪካችንን እንደ መስታወት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩን፤ ዛሬ ላይ ቆመን ነገ

ሁለንተናዊ ልዕልና ያላትን ሀገራችን ከነክብሯ እንደምትቀጥል የሚያመላክቱን አንጡራ ሃብቶቻችን ናቸው፡፡ እንደ ሕዝብ ከዚህኛው ዘመን የተሻገሩትን ድንቅ ስጦታዎች ዕውቅና መስጠት ይገባናል።

ያለፉትን ጊዜያት ማስታወስ፣ አሁን ያለውን ማኅበረሰብ በድር እና ማግ እንደማያያዝ ይቆጠራል።

ይሄንን በማድረግም ታላቅ ሕዝብ እንድንሆን ላደረጉን አባቶቻችን አክብሮት እንዲቸራቸው ያደርጋለን።

የኢትዮጵያ የፊደል ልዩ የሆኑት የኢትዮጵያ ፊደላት ለሀገራችን ጥንታዊ ሥልጣኔ የማያጠራጥር ኪዳን መሆናቸው ላይ ነው። ድርጅታችን የኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት (Ethiopian Social Partnership Advocacy)

ፊደልን በሚያከብርበት ዓመታዊ በዓል ሁሉ ማስተላለፍ የምንፈልገውን ዋና መልእክት አብሮነትንና አንድነትን ማዳበር ሲሆን በስሜት እና በጭፍን ጥላቻ ከፊደል የመሽሽ ሁኔታ ታርሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ብሔርብሔረሰቦች ውይይት አድርገው እንዲጠቀሙ እናበረታታለን ።

በስሜትና በጭፍን ጥላቻ ከፊደል የመሽሽ ሁኔታ ታርሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ብሔር ብሔረሰቦች ውይይት አድርገው እንዲጠቀሙ እንሠራለን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊደል በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ውይይት እንዲደረግበት በአጽንኦት እንጠይቃለን።

የተለያዩ ትምህርታዊ የሆኑ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ፣ ምሁራዊ መጣጥፎች በመዳሰስ ፣ እንዲሁም በተለያዩ ስመ ጥር በሆኑ ባለሙያዎች ውይይቶች እንዲደረጉ እንጠይቃለን ።

ያለፈውን የአሁኑን እና የወደፊቱን በማስተሳሰር ፣ ሀገራዊ መስተጋብር በመፍጠር ፊደላትን የሚያክል ማን አለ ??

የኢትዮጵያን የፊደል ዳግም የአገራችንን የድምቀት ባህል መድረክ መቀላቀሉ ፋይዳው ትልቅ ነው ፡፡

ይህን ልዩ የሆነ ታሪካዊ ኹነት በልዩ የታሪክ መዝገብ ላይ በደማቅ ቀለም ማስፈር ተገቢና አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም።

ከዚህም ባሻገር የፊደል ቀን ተውስኖ መከበሩን የሚናፍቁ፣ ደጋፊዎች፣ ተባባሪዎች፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወደውና የሚመተማመነው የወላጆቹ ሥራ የሚዘከርበት ቀን በይፋ ሊያውቅና ሊበሰርየተገባ ነው፡፡

በመሆኑ ፊደላችን ለአገራችን ያለውን ጠቀሜታ በውል ተገንዝቦ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲጠቀሙበት ማድረግ የአንድነታችን ማገር ያስተሳሰራል ብሎ ድርጅታችን የኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ ትስስር አነቃቂ ድርጅት (Ethiopian Social Partnership Advocacy) ያምናል ፤ ለዚህም ተፈጻሚነት በጽናት ይታገላል።

ከሰላምታ ጋር

ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

7:-02/10/2017

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

C-ESPA/0001/27

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...