የአቶ ታምራት ላይኔ ሹመት

Date:

አቶ ታምራት ላይኔ የዓለም አቀፍ የብሎክቼይን አስተዳደር አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ታምራት ላይኔ አድማሱን የሾማቸው ኩላዳኦ የተሰኘው የክሪፕቶ ከረንሲ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ አቶ ታምራትን ለምን እንደመረጣቸው ሲገልፅ ኢትዮጵያ ከአምባገነን መንግስት ወደዲሞክራሲ በምትሸጋገርበት ወቅት የተቋማት ግንባታና እርቀ ሰላም ላይ ትልቅ ሚና በመጫወታቸው እንደሆነ አስረድቷል፡፡

ከዚህ ልምዳቸው በመነሳት አሁን ደግሞ ድርጅቱ እያደገ በመጣው አዲሱ የክሪፕቶ ገበያ በመንግስታት ውስጥ ለመስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ያግዛሉ የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

አቶ ታምራት ላይኔ ሹመቱን ከተቀበሉ በኋላ ሲናገሩ ‹‹አስተዳዳራዊ ውድቀቶች እምነትን መልሶ በመገንባት ስራ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳላቸው የመጀመሪያ የአይን ምስክር ነኝ፡፡ ኩላ ዳኦ የአለማችን የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ ባልሆነበት በዚህ ዘመን ይህን ለማስተካከል የሚጥር ድርጅት በመሆኑ አብሬው ለመስራት ወስኛለሁ›› ብለዋል፡፡

ድርጅቱ በክሪፕቶ ከረንሲ አማካኝነት የተለያዩ የልማትና የእርዳታ ስራዎችን የሚያከናውን እንደሆነ በድረ ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...