ሜሮን ሶርኔሳ
ሜሮን ሶርኔሳ የ20 ዓመት ወጣት ስትኾን፣ የሕይወት ክህሎቷን ለማሳደግ በማለም በከፍታ የወጣቶች ፕሮጀክት በኩል የለውጥ ጉዞን ጀምራለች። ሜሮን የከፍታን የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ከመውሰዷ በፊት፣ ከሰዎች ጋር ትርጉም ያለው ንግግር የማድረግም ኾነ ሐሳቧን እና ስሜቷን በብቃት ለመግለጽ የሚያስችል ክህሎት እንዳልነበራት በግልጽ ትናገራለች። እንዲህ ያለው የራስ መተማመን እጦት እና የራስን ዐቅም በትክክል የማወቅ ችግር፣ ሜሮን በሕይወት ግቧ እና መሻቷ ላይ እርግጠኛ እንዳትሆን አድርጓት ቆይቷል።
ኾኖም የከፍታ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ለሜሮን ትልቅ ለውጥ አምጥቶላታል። በዚህ ሥልጠና፣ ሜሮንም ኾነች ጓደኞቿ ራሳቸውን በትክክል ከማወቅ ጀምሮ፣ ስለ ሕይወት ግቦቻቸው ግልፅ መረዳት እንዲኖራቸው አድርጓል። ከዚህም ባሻገር ሥልጠናው ለእነ ሜሮን ለሕይወታቸው የግል እቅድ እንዲያወጡ አስችሏቸዋል፣ ይህም ወደ ስኬት የሚወስደውን መንገድ በቀላሉ እንዲቀይሱ አስችሏቸዋል። በክህሎት ሥልጠናው የጨበጡት ሐሳብን የመግለፅም ኾነ በልበ ሙሉነት የመናገር ችሎታ በግል ለሚያደርጉት የዕድገት ግስጋሴም ትልቅ መነሳሻ ኾኖላቸዋል።
በተጨማሪም የከፍታ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ሜሮንን አስፈላጊ የሆኑ የአእምሮ ልህቀት እና የግጭት አፈታት ክህሎትን የተመለከተ ግንዛቤንም አስታጥቋታል። ሰልጣኞቹም በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የሚያጋጥሙ ግጭቶችን በራሳቸው ለመምራት እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፍታት ትምህርት ጨብጠዋል።
በዚህ መልክ ያገኙት አዲስ የሚባል ግንዛቤ እና ክህሎት ደግሞ፣ ለተሻለ የእርስ በርስ ግንኙነት መንገድ ከመጥረግ ጀምሮ፣ ሜሮን ማናቸውንም ፈታኝ ሁኔታዎች በቀላሉ እና በብቃት እንድትቆጣጠር አስችሏታል።
ዛሬ ላይ ሜሮን ለግሏ በደረሰችበት እድገት እና ብቃት ለሌሎች አንፀባራቂ ምሣሌ መኾን ችላለች። ሰልጣኞቹም ከሰዎች ጋር በብቃት የመግባባት፣ ሐሳብን በልበ ሙሉነት የመግለፅ እንዲሁም ስሜቶችን እና ግጭቶችን የመቆጣጠር ክህሎቶችን ጨብጠዋል። የወጣቶች ከፍታ ፕሮጀክት የሜሮንን ሕይወት ከመቀየር ባለፈ የሕይወት ዓላማቸውን እና ምኞቶቻቸውን እንዲሳኩ አስፈላጊውን መሠረት አደላድሎላቸዋል።
ሜሮን የተቀናጀ የወጣቶች እንቅስቃሴ – ከፍታ ፕሮጀክት የሕይወት ክህሎት ሥልጠና እንድትወስድ ዕድል ስለሰጣት ከልብ ታመሠግናለች። ሥልጠናው እነሱን ከማብቃት አልፎ፣ ለአዳዲስ እድሎች እና ለራሳቸው እና ሙያዊ ስኬታቸው ማለቂያ የሌላቸው በሮች ከፍቶላቸዋል። እናም አሁን ላይ ሜሮን፣ በአዲስ እምነት እና ግልጽ በሚባል የሕይወት ፍኖት መጪውን ጊዜዋን በዓላማ እና በቁርጠኝነት ለመምራት ተዘጋጅታለች።
———-
ቅጽ 6 ግዮን ቁጥር 219 ሕዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም
