የአዉሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 በፖላንድ ትራዝንኪ አሬና  Stadion Wrocław በቼልሲ እና ሪያል ቤቲስ መካከል ይደረጋል

Date:

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአህጉራዊ መድረክ  በሻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ሁለት ጊዜ ዋንጫዉን ማሳካት ሲችል  እንዲሁም ከ1960_1999 ድረስ ይከናወን በነበረዉ የዩሮፒያን ዋንጫ አሸናፊ ዋንጫ  በ1971 እና 98 የዉድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።

የአንዳሉሲያዉ ክለብ ሪያል ቤቲስ በአህጉራዊ መድረክ ዋንጫ ማሳካት ያልቻለ ሲሆን 2021 ላይ በአዲስ ቅርፅ ጅማሬዉን ባደረገዉ እና  በዕለቱ በሚያደርጉት የኮንፍረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንግሊዝን በመወከል ዌስትሀም ድል ማድረግ የቻለ ሲሆን በቀሪዎቹ አመታት ሮማ እና ኦሎምፒያኮስ የዉድድሩ አሸናፊዎች ናቸዉ።

በሊግ ዉድድር ቼልሲ ባለፈዉ ዓመት ከሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ዉጭ ሆኖ ያሳለፈ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ በመጪዉ ዓመት የመድረኩ ተሳታፊ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።

ሪያል ቤቲስ በአንፃሩ በስፔን ላሊጋ 6ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በቀጣይ አመት የዩሮፓ ሊግ ዉድድር ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

ከጨዋታዉ በፊት የቼልሲዉ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ባለቤቴን የተዋወኳት በሴቪያ ነዉ የመጀመሪያ ልጄ የተወለደዉ በሴቪያ ነዉ ለሴቪያም ተጫዉቻለሁ እናም ዋንጫዉን ማሸነፍ እንደምፈልግ ግልፅ ነዉ ኮንፍረንስ ሊግን በማሸነፍ  ለክለቡ እና ለደጋፊዎች ሁሉንም የአዉሮፓ ወድድሮች ያሸነፈ የመጀመሪያዉ ክለብ መሆን ማሳየት እንፈልጋለን የኮንፍረንስ ሊግ ዋንጫ የአሸናፊነት ባህርይን ለመላበስ መነሻ ይሆነናል እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎችን ለማሳካት ተነሳሽነትን ይፈጥርልናል ያሉ ሲሆን የተጨዋቾችን ወቅታዊ የማሸነፍ ስነልቦና በተመለከተ ጥሩ ስሜት ላይ ይገኛሉ በፕ/ሊግ ታሪክ ወጣቱን የቡድን ስብስብ ነዉ የያዝነዉ ነገር ግን የተለያዩ ዉድድሮች ናቸዉ ብለዋል።

ማሬስካ በእግርኳሱ ዘርፍ በሁለት አጋጣሚዎች ከፔሌግሬኒ ጋር ያሳለፉ ሲሆን በተጨዋችነት ፔሌግሬኒ ማላጋን እያሰለጠኑ እርሳቸዉ በተጨዋችነት ያሳለፉ ሲሆን በሌላ አጋጣሚ ፔሌግሬኒ ዌስትሃምን ሲያሰለጥኑ በምክትል አሰልጣኝነት አብረዉ ሰርተዋል።

ማሬስካም ፔሌግሬኒን በእግርኳስ እንደ አባቴ ነዉ የምቆጥራቸዉ አሁን ለምገኝበት ቦታ እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ ለ4 ዓመታት ከፔሌግሬኒ ጋር ስቻለሁ 2 አመት በተጨዋችነት 2 ዓመት በአሰልጣኝ አባልነት ባለን ግንኙነት እና ለሚሰጠኝ ምክር ትልቅ አክብሮት አለኝ ሁልጊዜ ይህን ይለኛል ትልቁ ነገር ምንጊዜም እዉነተኛ እና ራስህን መሆንህ ነዉ።ለሴቪያ ለ4 አመታት ተጫዉለሁ ሪያል ቤቲስ እና ሴቪያ ደግሞ በርካታ ደጋፊ ያላቸዉ  በስፔን ከትልቅ ደርቢዎች አንዱ ነዉ ብለዋል።

በቼልሲ በኩል በፕ/ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ በቅጣት ያልነበረዉ ኒኮላስ ጃክሰን ወደ ሜዳ ይመለሳል።

አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሬኒ በበኩላቸዉ ለኤንዞ ማሬስካ
በዉድድር ዓመቱ መጀመሪያ የኮንፍረንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ወቅት ለፍፃሜዉ አይሀለሁ ብየ አጭር መልዕክት ልኬለታለሁ እንዲሁም የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዉን ሲያሸንፍ ደዉየለታለሁ ያሉ ሲሆን በዌስትሃም እያለን በጋራ ስንሰራ ሁልጊዜም ስለእግርኳስ ነበር የምናወራዉ ስለዚህ ሁለታችንም ምን እንደምናስብ እናውቃለን ብለዋል።

በተጨማሪም በዛሬዉ የፍፃሜ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ዋንጫዉን የማሳካት ተመሳሳይ ዕድል አላቸዉ ከመጀመሪያዋ ደቂቃ ጀምሮ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን በማለት ቺሊያዊዉ የሪያል ቤቲስ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሬኒ ተናግረዋል።

በዉድድሩ ፑሉሉንዐን በመከተል ባካምቡ ከሪያል ቤቲስ በ8 እንዲሁም ማርክ ጉይ በ6 ጎሎች በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሲከተሉ በጥር ነዝዉዉር መስኮት ከማንችስተር ዩናይትድ በዉሰት በሪያል ቤቲስ ያቀናዉ አንቶኒ በኮንፍረንስ ሊግ 4ጎሎችን አስቆጥሮ 3 ለጎል የሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።

የምሽቱን የፍፃሜ ጨዋታ የ40 ዓመቱ  ቦስኒያዊዉ አርቢትር Irfan Peljto ይመሩታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...