የአዋሽ ወንዝ ሙላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከመኖሪያቸዉ አፈናቀለ

Date:

የተፈናቃዮች ቁጥር ከዘጠኝ ሺህ በላይ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኮምንኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ኤቢሴ ተርፋ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት የዛሬን ማለትም የነሀሴ 1 ቀን 2017 ዓ .ም መረጃን ሳይጨምር ከወንዙ መሙላት ጋር በተያያዘ ከዘጠኝ ሽህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የተፈናቀሉት ዜጎችም በሁለት ወረዳዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው የምግብ እና የመኝታ እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

” አሁንም የውሃው መጠን እየጨመረ ነው ” ያሉት ኃላፊዋ ከፍተኛ ትኩረት ይሻል ሲሉም አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...