ፕሬዚዳንቱን ለጠቆመ 50 ሚሊዮን ዶላር

Date:


አሜሪካ የቬንዙዌላውን ፕሬዚዳንት ያሉበትን ለጠቆመ 50 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች።

ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የአሜሪካ አስተዳደር ፍላጎት ካሳደረ ዋል በርካታ ጊዚያት ነጉደዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ጥር ላይ 25 ሚሊዮን ዶላር ፕሬዚዳንት ማድሮንን ለያዘ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

ትራምፕ አሁን ላይ ሽልማቱን በእጥፍ የጨመሩት ሲሆን የቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት በዓለም ላይ
ቁልፍ ከሚባሉ መሪ የህግ ወጥ አደንዛዥ ዕጽ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መካከል ናቸው በሚል ይከሳሉ።

ወደ አሜሪካ “ኮኬይን ” ሳይቀር እንዲገባ ያደርጋሉ የሚል ውንጀላ የሚቀርብባቸው ማዱሮ “ለምዕራቡ ዓለም አለመሽነፋችን ያሰጠን ስም ነው” በሚል ክሱን አይቀበሉትም።

የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ከማዱሮ ጋር ትስስር ያላቸው ከ$700 ሚሊዬን በላይ ሀብት፣
፡- ሁለት የግል ጀቶችን፣ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችን እና ብዙ ቶን “ኮኬይን” ጨምሮ ይዣለሁ የሚል መግለጫ ሰታለች።

አሜሪካ ታይቶ የማይታወቅ የማሳሳት ስራ ላይ ተጠምዳለች ያለው የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “በጄፍሪ ኤፒስቴን ምክንያት ትራምፕ የተነሳባቸውን ተቃውሞ እና ክስ ትኩረት ለማስለውጥ ያረጉት ነው “የሚል ምላሹን ይፋ አድርጓል። ዘገባው የአልጀዚራ ነው

NBCEthiopia

ሆኖ_መገኘት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...