የጀርመን ፣ፈረንሳይና ብሪታንያ መሪዎች በዪክሬን ጉዳይ ላይ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መከሩ፡፡
የጀርመኑ ፍሬድሪክ ሜርዝ፣የብሪታንያዉ ኬር ስታርመር እና የፈረንሳዩ ማክሮን በስልከ ትራምፕን አዉርተዋቸዋል፡፡
በዩክሬን ሰላም እንዴት መምጣት እንዳለበት ዉይይት ያደረጉት መሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ለማምጣት ቃል ገብተዋል፡፡
በሚቀጥሉት ቀናት በርካታ የድርድር ስራዎች እንደሚከወኑም መሪዎቹ ተወያይተዋል፡፡
ለዩክሬን እና ዩሮ-አትላንቲክ ቀጠና ወሳኙ ጊዜ ነዉም ብለዋል መሪዎቹ፡፡
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አዲስ ዕቅዳቸውን በተደራዳሪዎቻቸው አማካኝነት ለአሜሪካ ያቀርባሉ ተበሏል፡፡
የአዉሮፓ መሪዎች የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራም የሰላም ውጥን ለሩሲያ ያዳላ ነው በሚል መተቸታቸዉን ተከትሎ አዲስ የሰላም ሀሳብ ለመተግበር እየሰሩ ይገኛል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ለመፍትሄ እየሰራለሁ ማለታቸዉም አይዘነጋም፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነዉ፡፡
