የኢራን እና አይ ኤ ኢ ኤ ውዝግብ

Date:

ኢራን ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ድርጅት በትክክለኛ መርህ ላይ መቆም አለበት በሚል አስጠነቀቀች።

ድርጅቱ  (IAEA)  በአንድ አፍ ሁለት ምላስ “ደብል ስታንዳርድ” ዓይነት አካሄዱን መተው አለበት ባይ ናት ኢራን።

በቴህራን የኑክሌር መርሃ ግብር  ዙሪያ ትብብር ከተፈለገ ራፋኤል ግሮሲ መራሹ አይ ኤ ኢ ኤ ፍትሃዊ አካሄድ ሊኖረው እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን  ለአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ የኢራን ከድርጅቱ ጋር መተባበራችንን  የምንቀጥለው አንዱን ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የሚደረጉ ጥረቶች ሲቆሙ ብቻ ነው ብለዋቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኢራን ላይ ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ አደገኛ ምላሽ እንሰጣለን በሚልም አረጋግጠዋል።

“ለጥቃቱ ምላሽችን ጠላቶቻችን የሚጸጸቱበት ይሆናልም “ባይ ናቸው ማሱድ ፔዜሽኪያን።

በቴህራን እና በአይ ኤ ኢ ኤ መካከል የነበረው ትብብር ከመቋረጡም ባሻገር በአሁኑ ሰዓት ፖለቲካዊ መካሰስ ውስጥም ናቸው።

በተለይም በ12 ቀናቱ ጦርነት የድርጅቱ ቁመና ወላዋይ ነበር የሚል ቅሬት ቴህራን በተደጋጋሚ እያቀረበች ይገኛል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ዘግቦታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...