የኢሶዴፓ 309 ዕጩዎች ከውድድር ውጪ የተደረጉበት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ

Date:

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ ችሎት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) 309 ዕጩዎችን ከውድድር ውጪ ያደረገበትን ውሳኔ  አፀና።

ቦርዱ በፓርቲው አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታጥ የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ፣ በኢሶዴፓ ለሕዝብ ይፋ ተደርገው የነበሩት ዕጬዎች “ምርጫ ላይ እንዳይሳተፉ ከውድድሩ ውጭ” መደረጋቸውን አስቀድሞ ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ “የዜጎችን መሠረታዊ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊነጥቅ አይገባም” ያለው በፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር የሚመራው ቡድን ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ “የምርጫው ሂደት ቆሞ ከዕጩ ምዝገባው ጀምሮ የተፈፀሙ” ያላቸው “የሕግ ጥሰቶች” ታርመው ሐቀኛ እና ተዓማኒ ምርጫ እንዲከናወን ጠይቋል።


በፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ራሔል ባፌ የሚመራው ኢሶዴፓ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተወዳዳሪ ሆነው ተመዝግበው የቀረቡ 309 ዕጬዎችን ለሕዝብ ይፋ ቢያደርግም በዕጩዎቹ ላይ በእነ አቶ አጫሞ ቦቄ በኩል ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በመቅረቡና “ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎች በሕግ አግባብ ሊስተናገዱ ይገባል” በሚል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመወሰኑ ዕጩዎቹ ከውድድር ውጪ መደረጋቸውን ቀደም ብሎ አስታውቋል።

ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ለዶቼ ቬለ የገለፁት ዶክተር ራሔል ፍርድ ቤት ይህንኑ የቦርዱን ውሳኔ ማጽናቱን ነግረውናል። ውሳኔዉም “የፓርቲውን ሕልውና ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ የጀመረችውን የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት በእጅጉ የሚፈታተን ነው።”ብለውታል።

በእነ አቶ አጫሞ ቦቄ በኩል ቀርበው ነበር የተባሉ ዕጩዎችም በፍርድ ቤት ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ፓርቲው ከቀናት በኋላ በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ አይሳተፍም።

“የሰበር የመጨረሻ ይግባኙ ያለ ሥልጣኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነውን ነው ያፀደቀው። ግን [ጉዳዩ] የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ውሳኔ ነው” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...