የውጤት ተቀባይነት፡ የዴሞክራሲያዊ ብስለት ማረጋገጫ

Date:


ግዮን መጽሔት
:- ምርጫ ውድድር እንደመሆኑ፣ አሸናፊና ተሸናፊ መኖሩ የማይቀሬ ነው። እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚፈተነው ደግሞ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ በሚታየው ምላሽ ነው።


የሕዝብን ፍላጎት ማክበ
ር፦


የምርጫው ውጤት እኛ ከምንፈልገው ዕጩ ወይም ፓርቲ በተቃራኒ ሊሆን ይችላል። ውጤቱ በገለልተኛ ታዛቢዎችና በምርጫ ቦርድ ተዓማኒነቱ ከተረጋገጠ፣ የሕዝብን ድምፅ አክብሮ መቀበል ለሰላም ግንባታ ወሳኝ ነው። “እኔ ካልመረጥኩት በቀር ውጤቱን አልቀበልም” የሚል አቋም ለግጭትና ለአገራዊ ቀውስ በር ይከፍታል።
ቅሬታን በሕጋዊ መንገድ መፍታት፦


በሂደቱ ላይ ቅሬታ ካለ፣ ይህንን ቅሬታ በኃይል ወይም በብጥብጥ ሳይሆን፣ በሕግ በተቀመጡ መንገዶች (በምርጫ ቦርድ ቅሬታ ሰሚ አካላት ወይም በፍርድ ቤት) መፍታት የሥልጣኔ መገለጫ ነው። ሕጋዊነትን መከተል ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና ለዘላቂ ሰላም ዋስትና ነው።


የአሸናፊዎችና የተሸናፊዎች ኃላፊነት፦


አሸናፊው ወገን የተሸናፊውን ወገን ደጋፊዎች በማክበርና በማካተት መንቀሳቀስ ሲኖርበት፣ ተሸናፊውም ውጤቱን በጸጋ በመቀበል ለቀጣይ ምርጫዎች ራሱን በሰላማዊ መንገድ ማዘጋጀት ይኖርበታል። ይህ ዑደት ነው አገርን ወደ ተረጋጋ ዴሞክራሲ የሚያሻግረው።


4. የወጣቶች ሚና፡ የሰላምና የሥርዓት ጥበቃ ስትራቴጂ


ወጣቶች የኢትዮጵያ ግዙፉ የሕዝብ ክፍል ብቻ ሳይሆኑ፣ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን የማድረግ ትልቁን ኃላፊነት የተሸከሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናቸው።


እንደ ሰላም ዘበኝነት፦


ወጣቶች በምርጫ ዕለት በጣቢያዎች አካባቢ የሚታዩ ስሜታዊ እንቅስቃሴዎችን በማረጋጋት፣ ሕዝቡ በሥርዓት ድምፅ እንዲሰጥ በማገዝ እና የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው። ወጣቱ ለጥፋት ሳይሆን ለልማትና ለሰላም የቆመ መሆኑን የሚያሳይበት ትልቁ አጋጣሚ የምርጫ ዕለት ነው።


የሐሰት መረጃን መመከት፦


በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱ የሐሰት ወሬዎች በምርጫ ዕለት ግጭት እንዲቀሰቀስ ሊያደርጉ ይችላሉ። ቴክኖሎጂን የሚረዳው ወጣት፣ እነዚህን መረጃዎች በማጣራትና ትክክለኛውን መረጃ በማሰራጨት ማኅበረሰቡን ከብጥብጥ የመጠበቅ ሞራላዊ ግዴታ አለበት።


የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ፦


ወጣቶች ዛሬ የሚያሳዩት ዲሲፕሊንና ለዴሞክራሲያዊ እሴቶች ያላቸው ታማኝነት፣ ነገ ለሚረከቧት ኢትዮጵያ መሠረት ነው። በምርጫ ዕለት በነቃ ተሳትፎ ድምፅ መስጠትና ውጤቱን በሰላም መቀበል፣ የወጣቱን ፖለቲካዊ ብስለት ለዓለም የሚያሳይ ተግባር ነው።
ጠቃለያ


ውድ ኢትዮጵያዊያን መራጮች፤


የምርጫ ካርድዎ የነገዋ ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነው። ይህ ካርድ ትርጉም የሚኖረው ግን በምርጫ ዕለት ወደ ምርጫ ጣቢያ ሄደው ድምፅዎን በሳጥኑ ውስጥ ሲያሳርፉ ብቻ ነው። ድምፅ መስጠት የግል መብት ቢሆንም፣ ውጤቱ ግን አገራዊ ነው።


በምርጫ ዕለት የምናሳየው ዲሲፕሊን፣ ለሕግና ለሥርዓት የምንሰጠው ክብር፣ እንዲሁም የምርጫውን ውጤት በሰላማዊ መንገድ የመቀበል ዝግጁነታችን ለዓለም የምናሳየው የዴሞክራሲ መታወቂያችን ነው።

በተለይም ወጣቶች፣ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም ለሰላምና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላችሁን ቁርጠኝነት በተግባር እንድታሳዩ ዩዝ ኤንድ ከልቸራል ዴቨሎፕመንት ፋውንዴሽን (YCDF) ጥሪውን ያቀርባል።


በምርጫ ዕለት በአካል እንገኝ! በዲሲፕሊን ድምፃችንን እንስጥ! ውጤቱን በጸጋ እንቀበል!

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን (Youth and Cultural Development Foun
dation – YCDF) ከአውሮፓ የምርጫ ድጋፍ ማዕከል (ECES)  ጋር በመተባበር ነው።

የወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት፣ ባህላዊ እሴቶችን በማሳደግ፣ የሰላም
ግንባታ ሥራዎችን በማስፋፋት እና የወጣቶችን ንቁ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በማጎልበት ላይ በትኩረት የሚሠራ ገለልተኛ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሒደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ግንዛቤ በመፍጠርና አቅማቸውን በማጎልበት የላቀ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር 234  ግንቦት 2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...