አየር መንገዱ በዩኤኢ ዋና ከተማ አቡ ዳቢ የሚያደርገውን ዕለታዊ በራራ ትናንት አስጀምሯል፡፡ መዲናዋ ከዱባይ እና ሻርጃ ቀጥሎ ተከታይዋ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መዳረሻ ሆናለች፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው “ወደ አቡ ዳቢ የጀመርነው አዲስ አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር ለማገናኘት የያዘውን ስትራቴጂያዊ እቅድ የሚያንፀባርቅ ነው” ብለዋል።
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ባህረ ሰላጤው ሀገራት 13 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሳምንት ከ100 በላይ የመንገደኞች በረራዎችን ያካሂዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
