የጉቴሬዝ ቁጣ በእስራኤል ላይ

Date:

የመንግስታቱ ድርጅት እስራኤል የሶሪያን ሉዓላዊነት እንድታከብር ጠየቀ።

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እስራኤል በደቡባዊ ሶሪያ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከድርጊቷ እንድትቆጠብ አሳስበዋል፡፡

ጉቴሬዝ ቀጠናዊ ውጥረቱ እንዳይስፋፋ ስጋት አለኝ በሚልም አስጠንቅቀዋል።

እስራኤል የሶሪያን ሉዓላዊነት እና ግዛት አንድነት እንዲሁም ነጻነት መጣስ የለባትም በሚል ያስጠነቀቁት ጉቴሬዝ፣ በቃል አቀባያቸው በኩል ድርጊቱን አግባብነት የለውም ሲሉ  ኮንነውታል፡፡

በደቡባዊ ሶሪያ በአብዛኛው ድሩዝ በሚበዛበት ሱዋይዳ ግዛት የተቀሰቀሰውን ግጭትም አውግዘዋል ጉቴሬዝ።

ከሰላሳ በላይ ሰዎች በዚህ ግጭት ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሶሪያ የተፈጠረው አለመረጋጋት የእስራኤል ጦር በጎላን ተራሮች አካባቢ ያለውን ግዛት ለማስፋት እንደመልካም አጋጣሚ ይጠቀምበታል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...