የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ፍጥነት በመጨመሩ አደጋ እያጋጠመ ስለሆነ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ያድርግ

Date:

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የባቡር ፍጥነት በሰዓት ከነበረበት 37 ኪሎ ሜትር ወደ  60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው÷የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ በቀን የነበረውን የምልልስ መጠን ከሁለት ወደ ስምንት አሳድጓል፡፡፡

የባቡሩ የፍጥነት መጠኑም በፊት ከነበረው በሰዓት 37 ኪሎ ሜትር ወደ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አመልክቷል፡፡

የባቡሩ ፍጥነት መጨመሩን ተከትሎ ሕብረተሰቡ የፍጥነት መሻሻሉን ባለመገንዘብ ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

ስለሆነም በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የባቡሩ ፍጥነት ከዚህ በፊት ከነበረው መጨመሩን በመገንዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማህበሩ አሳስቧል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ከዚህ በፊት ጉዳት ሲደርስ ይሰጥ የነበረውን የካሳ ክፍያ ማቆሙንም አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...