የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ላይ መሳተፍ ጀመረ

Date:

ብሄራዊ ባንክ እያደረገ ካለው ለውጥ መካከል የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታን ማዘመን እና ከፋይናንስ ኩባንያዎች ባሻገር ተጨማሪ ተጫራቾች እንዲሳተፉ መሳብ ይገኝበታል፡፡

በዚህም መሰረት ግዙፍ የመንግስት ቢዝነስ ተቋማተትን የያዘው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲን በየ15 ቀኑ በሚደረገው የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ (የመጀመሪያ ደረጃ የገንዘብ ገበያ) ተሳታፊ መሆን መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በዚህም በመጀመሪያው የጨረታ ተሳትፎ 7 ቢሊየን ብር የሚያወጣ ቦንድ መግዛቱን ነው የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ያስታወቀው፡፡

የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታን ለገንዘብ ሚኒስቴር በውክልና የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ሰነድ ተሸጦ የሚገኘው ገንዘብ ለበጀት ጉድለት ማሟያ የሚያገለግል ሲሆን በተለይ መንግስት ከብሄራዊ ባንክ የሚወስደውን የቀጥታ ብድር እንዲቀንስ ወይም እንዲያቆም የሚያግዝ በመሆኑ የዋጋ ንረትን ለመከላከል አይነተኛ መሳሪያ መሆኑ ይነገርለታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...