ግብፅ የፍልስጤም መንግስት እስካልተመሰረተ ድረስ ከእስራኤል ጋር የጠበቀ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደማይኖር አስታወቀች፡፡
ካይሮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላት ግን ከመገልጽ አልተቆጠበችም፡፡
ግብጽ በህዝብ ደረጃ የሚደረግ መደበኛ ግንኙነት ሊኖር የሚችለው በፍልስጤም ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት ሲደረስ ብቻ መሆኑንም ይፈ አድርጋለች።
ምንም እንኳ ግብፅ እና እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቢኖራቸውም፣ ህዝባዊ ትስስሩ የሚጸናው፤ የፍልስጤም ጉዳይ መፍትሄ ከማግኘቱ ጋር የተያያዘ መሆኑ ሀገራቱ ውዝግብ ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል።
ይህ የግብፅ አቋም፣ በቀጠናው እየተከሰቱ ያሉ የፖለቲካ ለውጦችን የሚያሳይ እና የሀገሪቱን የውጭ ፖሊሲ የሚያንፀባርቅ ነው ተብሏል።
ግብፅ የ1967ቱ የድንበር መካለልን ተከትሎ ሉዓላዊ የፍልስጤም መንግስት እንዲቋቋም ትፈልጋለች፡፡
ቲ አር ቲ እንደዘገበው፡፡
