የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ የሚያካሂደው “ዘመቻ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሸጋገረ”

Date:

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ወደ “ቀጣዩ ምዕራፍ እየተሸጋገረ” መሆኑን እና የቴህራን “አገዛዝን እና ወታደራዊ አቅምን ከዚህም የበለጠ የመበታተን” እርምጃውን እንደሚገፋበት ገለጸ።

አሜሪካ እና እስራኤል በሚፈጽሙት ጥቃት ኢራንን “በስትራቴጂካዊ መንገድ እየነጠሉ” መሆኑን የተናገሩት የእስራኤል ጦር ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ኢያል ዛሚር፤ “ከዚህ ቀደም ባይታየ ደረጃ” እያዳከሟት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

እስራኤልባለፉት ስድስት ቀናት “ያለ ማቋረጥ” ኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጸም መቆየቷን አንስተው፤ “ዘመቻው ባቀድነው ፍጥነት እየሄደ ነው” ብለዋል።

ዋና አዛዡ ባወጡት መግለጫ “የአየር የበላይነትን ያረጋገጥንበትን እና የባለስቲክ ሚሳዔል መሠረታቸውን ያዳከምንበትን ድንገተኛ የጥቃት ምዕራፍ ካጠናቀቅን በኋላ፤ አሁን ወደ ቀጣዩ የዘመቻ ምዕራፍ እየተሸጋገርን ነው” ሲሉ ዕቅዳቸውን አስታውቀዋል።

“በዚህ ምዕራፍ የኢራንን አገዛዝ እና ወታደራዊ አቅሙን የበለጠ እንበታትናለን። አሁን ይፋ የማላደርጋቸው ተጨማሪ ድንገተኛ እርምጃዎች ወደፊት እንወስዳለን” ሲሉም ጽፈዋል።

ወታደራዊ አዛዡ የሊባኖስንም ጉዳይ ባነሱበት በዚህ መግለጫ፤ ሄዝቦላህ ጦርነቱን መቀላቀሉ “ስትራቴጂካዊ ስህተት” እንደሆነ ገልጸዋል። እስራኤል በጦርነት “ግንባርም ሆነ ሊባኖስ ውስጥ በጥልቅ በመግባት በኃይል እያጠቃች” መሆኑን ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...