የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ለአመታት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።
የእስራኤል ጦር ኃይል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ኢያል ዛሚር ከቅርብ ወራት ወዲህ ይህ የጥቃት ዝግጅት “ከበድ ባለ ሚስጥራዊ ሁኔታ” እንዲፋጠን ተደርጓል ብለዋል።
ዝርዝር መረጃ ያልሰጡት ኤታማዦር ሹሙ ወታደራዊ ዘመቻው ሊሳካ የቻለው “ተግባራዊ እና ስትራቴጂካዊ ሁኔታዎች በመጣጣማቸው ነው” ብለዋል።
አክለውም ይህ ጥቃት ቢዘገይ ኖሮ “እነዚህ ሁኔታዎች ሊታጡ እንደሚችሉ” እና እስራኤልን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።
“ለከባድ እና ድንገተኛ ጥቃት ምስጋና ይግባውና ድንቅ ውጤቶችን አስመዝግበናል” ብለዋል።
