የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 138.2 ብር ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል። ይህ ዋጋ ከአንድ ወር በፊት በ8ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 136.6 ብር ጋር ሲነጻጸር የብር ምንዛሪ ዋጋ መጨመሩን ያሳያል።
በዘጠነኛዉ ዙር ጨረታ 150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የቀረበ ሲሆን 28 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል አግኝተዋል፣ በአንጻሩ በ8ኛው ዙር ጨረታ ተጠቃሚ የነበሩት ባንኮች ቁጥር 11 ነበር።
ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ የሚካሄዱ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎች የሚወሰኑት በገበያው ሁኔታ ላይ በመመስረት መሆኑን ገልጿል። ቀጣይ ጨረታዎች ከመካሄዳቸው በፊት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቋል።
