“የዓድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ” ምስረታ እንደሚበሰር ተገለጸ

Date:



የዓድዋ ድልን ታሪካዊ ፋይዳ ለትውልድ ለማስተላለፍና የአፍሪካውያንን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል “የዓድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ” ለመመሥረት ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ እና በ130ኛው በዓል ለዓለም ይፋ እንደሚደረግ የተናገሩት ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ናቸው።

በ130ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ይፋ እንደሚደረግ የሚጠበቀው የተቋሙ ወደ ሥራ መግባት ዝርዝር መግለጫዎች እየተዘጋጁለት እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።

ይህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከታሪክ ዘካሪነቱ ባለፈ፣ የፓን አፍሪካኒዝም መንፈስን በተደራጀ የዕውቀት ዘርፍ ለማሳደግ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

ላለፉት 56 ዓመታት የዓድዋን ድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲያስተዋውቁ የቆዩት ፕሮፌሰር ማሞ፣ ድሉ በተለይም እሳቸው ሚያስተምሩበት የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ያሉ እና ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ

አፍሪካውያን ምሁራን በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ ላለፉት 11 ዓመታት በድምቀት ሲከበር እንደነበር አስታውሰዋል።
ድሉ በኬፕ ታውን እንዲከበር የተደረገበት ዋና ምክንያትም ነጮች ስለ ድሉ ጥልቀት እንዲረዱ፣ ጥቁሮች ደግሞ ከታሪካዊ ድላቸው እንዲማሩ እንደሆነ ምሁሩ አብራርተዋል።

በኬፕታውን ከተማ በሚካሄደው የምሁራኑ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ከተገኙ ታላላቅ ሰዎች መካከል የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ እምቤኪ እንደሚገኙበት ያስታወሱት ፕሮፌሰር ማሞ፣ 130ኛው የዩኒቨርሲቲው ምሥረታ ይፋ የሚደረግበት እንዲሆን እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲውን ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ምንጭ በተመለከተ፣ በራስ አቅም የመቆም ጽኑ አቋም ቢኖርም የድሉን ትርጉም የሚረዱ በርካታ አገራት ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ፍላጎት ማሳየታቸውና ንግግር እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል።

በአጠቃላይ “የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ” የምሥረታ እንቅስቃሴ፣ የዓድዋን ድል ከወታደራዊ ድልነት ወደ አህጉራዊ የልህቀትና የዕውቀት ተቋምነት ለማሸጋገር የሚደረግ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው ተብሏል።

(አሐዱ ራድዮ) 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአንድ ዓመት ውስጥ ቃል የተገቡ 417 የዓይን ብሌኖች ለሆስፒታሎች ተሰራጩ

​ የኢትዮጵያ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት...

በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው

በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ...

ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲሱ ዓመት 11 አዳዲስ የሙያ ትምህርት ዓይነቶችን ይፋ አደረገ

​የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል...

የአዲስ አበባ ጉዳይ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ የሚካሄደውን ምክክር ጥላ አጥሎበታል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ25ኛ ቀን ውሎው በሥራ ቡድን ደረጃ...