የዕዳ ሽግሽግ ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 2.8 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ትከፍል ነበር ተባለ

Date:

የኢትዮጵያ መንግስት ለ2017 በጀት ዓመት የነበረውን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በግልጽ አስቀምጧል። የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ እንደተናገሩት፣ ምቹ የዕዳ ማስተካከያ (ሽግሽግ) ባይኖር ኖሮ ሀገሪቱ በዚህ ዓመት ብቻ 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ ዕዳ መክፈል በግድ ይላት ነበር።

ይሁን እንጂ መንግስት በ G20 የጋራ ማዕቀፍ ውስጥ ከአበዳሪ አገራት ኮሚቴዎች ጋር ባደረገው ውጤታማ ድርድር 1.9 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ለመክፈል ተችሏል። ይህም የዕዳ ሽግሽጉ በግምት 1 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን እፎይታ እንዳስገኘላቸው ሚኒስትሯ አመልክተዋል።

በተጨማሪም በ2016 በጀት ዓመት መገባደጃ ላይ የሀገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ ከሀገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት (GDP) ጋር ሲነፃፀር 13.7 በመቶ እንደነበር ፍፁም አሰፋ ( ዶ/ር)  አብራርተዋል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት ከአበዳሪ ኮሚቴዎች ጋር ባካሄደው ገንቢ ውይይት በመርህ ደረጃ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የዕዳ እፎይታ ስምምነት ላይ ደርሷል።

ይህ ስምምነት እንደተገለፀው በ2017 የ 1.5 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2018 የ 400 ሚሊዮን ዶላር፣ በ2019 የ 500 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም በ2020 የ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ሽግሽግን ያካተተ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...